ማጠቃለያ

ለእያንዳንዳችን መዳረሻችንን አወቅነውም አላወቅነውም በሕይወት ጉዞ ላይ እንዳለን ግልጽ ነው። አሁን ያለንበት ደረጃ ላይ እንድንደርስ ያደረገን የቀድሞ ሕይወታችን ሲሆን አሁን በሕይወታችን የምናደረገው ነገር በሙሉ ደግሞ የወደፊት እጣፋንታችንን የሚወስን ይሆናል። ይህ “ጉዞ ወደ ክርሽና” ተብሎ የተሰየመው መፅሀፍ የተዘገበው፣ ከሰባተኛው የብሀገቨድ ጊታ መፅሀፍ ምዕራፍ ውስጥ በመምህር ከተሰጠው ንግግር የተወሰደ ነው። ይህ መፅሀፍ የሕይወታችን ከፍተኛው መዳረሻ ምን እንደሆነ የሚያመላክት እና ስለ ጉዟችን የመንፈሳዊ ትምህርቶች ገለፃ ላይ ትኩረት የሚያደረግ ነው።

ዓብዩ ጌታ ሽሪ ክርሽና ለትሁት አገልጋዩ አርጁና ስለ ሕይወታችን ዓላማ እና ጉዞ ሲያስተርምረው፣ ጉዟችንን ስኬታማ ለማድረግ የሚከተሉት ሁለት ነጥቦች ወሳኝ እንደሆኑ ገልፆለት ነበር።

1. በውስጣችን ያለው አመለካከት

2. የምንሰራቸው ነገሮች በሙሉ

በመሰረቱ ብዙ ሰዎች ከተገነዘቡት ወይም ከሚረዱት በላይ፣ ሕይወታችን ከፍተኛ ትርጉም ያላት እንደሆነች መረዳት ይገባናል። ይህንንም የሕይወታችን ትርጉም እና ዓላማ በትክክሉ መረዳት፣ መንፈሳዊ ሕይወታችን ስኬታማ እንዲሆን በትልቅ እርምጃ ሊያራምደን የሚችል ነው።

ይህ “ጉዞ ወደ ክርሽና” ተብሎ የተሰየመው መፅሀፍ፣ ልክ እንደ የጉዞ አውራ ጎዳና ንድፍ በጥንቃቄ የተዘጋጀ በመሆኑ ለእያንዳንዳችን ለዚህ ለተወሳሰበው ሕይወታችን ጥርት ያለ ትርጉም የሚሰጠን እና መዳረሻችን ምን መሆን እንደሚገባው የሚገልፅ ነው። የተካተቱትም ነጥቦች ሁሉ የተወሰዱት “ብሀገቨድ ጊታ” ተብሎ ከሚታወቀው እና በዓለም ውስጥ ቀዳማዊ ተብሎ ከሚታወቀው ራስን የማወቅ ጥናት መፅሀፍ ውስጥ ነው።

Synopsis  

We’re all on a path to somewhere, whether we have a destination in mind or not. Our past brought us to where we are today, and our present course creates our future. On The Way To Kṛṣṇa is a compilation of lectures on the seventh chapter of the Bhagavad-gītā that gives several meditations on life’s ultimate destination, from the spiritual point of view.

Kṛṣṇa, the supreme authority, is explaining to His disciple Arjuna that our life’s path depends on 1) our attitude and 2) our activities. Life has significantly more meaning and purpose than most people realize, and becoming aware of that purpose is a major step towards our spiritual self-fulfillment.

On The Way To Kṛṣṇa uses a “highway” metaphor (along with “roadmaps”) as a conceptual framework for understanding how each of us can discover our life’s intrinsic meaning and destination, based on the teachings of the Bhagavad-gītā, one of the world’s best known and oldest books of self-knowledge.